Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ...

32

Transcript of Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ...

Page 1: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን
Page 2: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Contents መግቢያ ............................................................................................................................................................................................ 2

ቢዝነስ ቲዋይሲ ሶፍትዌር ለማነው? .......................................................................................................................................... 3

ቢዝነስ ቲዋይሲ ታክስ ሶፍትዌር ጥቅሞች? ............................................................................................................................... 4

ማሰናዳት .......................................................................................................................................................................................... 5

የ Business TYCታክስሶፍትዌርለመጠቀም ............................................................................................................................. 5

መረጃ ማስገቢያ ............................................................................................................................................................................... 8

የሀገር ውስጥ እቃ ግዢ .........................................................................................................................................................9

የሀገር ውስጥ አገልግሎት ግዢ ............................................................................................................................................. 11

የሀገር ውስጥ አገልግሎት ግዢ ............................................................................................................................................. 11

ተ.እ.ታ ያልሆኑ /ተጨማሪ እሴት ታክስ/ (Non-VAT) ................................................................................................... 13

የሃገር ውሰጥ ሽያጭ ............................................................................................................................................................ 15

ዊዝሆልዲንግ ታክስ ..............................................................................................................................................................17

ተእታማመልከቻ /VAT REPORT/ ........................................................................................................................................ 18

የስራ ግብር .......................................................................................................................................................................... 25

የሰራተ ................................................................................................................................................................................. 25

የጡረታ መዋጮ ................................................................................................................................................................. 27

ተጨማሪ ድርጅቶችን/አካውንቶችን በመፈጠር ማስተዳደር ................................................................................................. 29

Page 3: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

2

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

መግቢያ BusinessTYC Tax በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የታክስ መረጃ መያዣ፣ ማዘጋጃ እንዲሁም ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

ታክስ ማሳወቂያ ሶፍትዌር ነው። BusinessTYC Tax ማንኛውም ሰው (የአካውንቲንግ እውቀት ያለው ወይም የሌለው)

እንዲጠቀመው በጣም በቀላል ዲዛይን ተደርጓል።

በመሆኑም ሶፍትዌሩን ለመጠቀም አካውንት መፍጠርና የየወሩን ሽያጭና ግዢ ብቻ ማስገባት በቂ ነው፡፡ እርሶ ካስገቡት

መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የሚገቡትን ዶክመንቶች ማለትም የሀገር ውስጥ ዕቃ ግዢ፣

የሀገር ውስጥ አልግሎት ግዢ፣ ተ.እ.ታ (ተጨማሪ እሴት ታክስ)፣ ዊዝሆልዲንግ ታክስ፣ የሰራተኛና የጡረታ ሪፖርቶችን እራሱ

ያዘጋጃል።

ከዚህ በተጨማሪ ሶፍትዌሩ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥቅሞች ይሰጣል፦

➢ ሶፍትዌሩ ወርሀዊ ተ.እ.ታ ሲያዘጋጅ ካለፈው ወር የዞሩ ሂሳቦችን ስለሚሰራ ለተገልጋዩ የታክስ አሰራር ስርአቱን እጅግ

በጣም ያቀልለታል፣

➢ በተጨማሪም ወርሀዊ የስራ ግብርና የጡረታ መዋጮ ፎርሞችን ሶፍትዌሩ እራሱ ያዘጋጃል፣

➢ በአጠቃላይ ሶፍትዌሩን በመጠቀም አሁን እስካሉበት ሰዓት ድረስ ያለውን የድርጅቶን ትርፍና ኪሳራ ማወቅ

ያስችሎታል።

➢ ሶፍትዌሩ እራሱ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ማስጠንቀቂያዎችና ማነቃቂያዎች በኢሜልዎ ይልክሎታል፣ ከነዚህ

ማስጠንቀቂያዎችና ማነቃቂያዎች መሐከል፦

o የቫት ማሳወቅያ ቀኖች፣

o የቫት ተከፋይ መጠን መብዛት፣

o የዊዝሆልዲንግ ክፍያ አለመሰብሰቡ፣

o አጠቃላይ የወር የግብር መጠን፣

o የበጀት አመቱን ትርፍና ኪሳራ በየወሩ

o የአመታዊ ተከፋይ መጠን ባላንስ አለማረግ፣

Page 4: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

3

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ቢዝነስ ቲዋይሲ ሶፍትዌር ለማነው? የቢዝነስ ቲዋይሲን ታክስ ሶፍትዌር ለመጠቀም መሰረታዊ የኮምፒውተርና የኢንተርኔት ችሎታ በቂ ሲሆን፡ የሚከተሉት ሶስት

ዋና ዋና አካሎች በሶፍትዌሩ ከፍተኛ ጥቅም ማግኘት ይችላሉ።

1. የሂሳብ ባለሞያዎች (አካውንታቶች)

ሒሳብ ለተለያዩ ድርጅቶች ሰርተዉ ለሚያሳውቁ የሂሳብ ባለሞያዎች (አካውንታቶች) እና የሂሳብ ባለሞያዎች ሶፈትዌሩን

በመጠቀም የብዙ ደንበኞችን የታክስ ማሳወቂያ ፎርሞችን ማዘጋጀት እና ማደራጀት ይችላሉ፣ በመሆኑም የደንበኛቸውን ቁጥር

መጨመር ይችላሉ።

2. የድርጅት ባለቤቶች

በዝቅተኛ ወጪና እንግልት የራሳቸውን ድርጅት ሂሳብ ማዘጋጀት፣ መቆጣጠርና ማሳወቅ የሚፈልጉ የድርጅት ባለቤቶች።

በተለይ የሚከተሉት አይነት የድርጅት ባለቤቶች ሶፍትዌሩን የሚጠቀሙ ሲሆን ከፍተኛም ጥቅም ያገኙበታል፦

● አካውንታንት ለመቅጠር አቅም ወይም ፍላጎት ለሌላቸው የድርጅት ባለቤቶች፣

● አካውንታንት ኖሯቸው የአካውንታንቱን ስራ መቆጣጠርና መረጃ በማንኛውም ሰአት ማግኘት ለሚፈልጉ፣

● አካውንታንት ኖሯቸው በአካውንታንቱ ስራ ደስተኛ ላልሆኑና ወጪ መቀነስ ለሚፋልጉ፣

● የመንግሰት ኦዲት በሚመጣ ጊዜ መጨናነቅ የማይፈልጉና በቅድሚያ በጥንቃቄ መረጃቸውን ማደራጀት

ለሚፋል፣

● የተለያየ ቦታ የሚጓዙና ድርጅታቸውን ከየትኛውም ቦታ መቆጣጠር የሚፈልጉ የድርጅት ባለቤቶች።

3. ስራን መጀመር ለሚፋልጉ ኢንተርፕሩነሮች

በመጨረሻም የሂሳብ ማዘጋጀትና ማሳወቅ ስራን መጀመር ለሚፋልጉ ኢንተርፕሩነሮች፣ ይህ ሶፍትዌር በቀላሉ ስራ እንዲጀምሩ

ያግዛቸዋል።

ከላይ እንደተጠቀሰው ቢዝነስቲዋይሲን ለመጠቀም ምንም አይነት የተለየ እውቀት አያስፈልገውም። በመሆኑም ይህን ማኑዋል

በማንበብ ወይም አጭር ስልጠና በመውሰድ አሁኑኑ መጠቀም ይችላሉ።

Page 5: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

4

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ቢዝነስ ቲዋይሲ ታክስ ሶፍትዌር ጥቅሞች? ማንኛውንም ሶፍትዌር መጠቀም ጥሩ ልምድ ሲሆን፣ ከሚሰሩት ስራ ጋር ቀጥተኛ ተዛማጅነት ያለውን ሶፍትዌር መጠቀም

ደግሞ እርሶና ድርጅትዎን ወደ ስኬት መንገድ ሊወስድ የሚችል ነው። ነገር ግን ከሚሰሩት ስራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለውን

ሶፍትዌር ማሰራት በጣም ከባድና ውድ ነዉ። አሁን ግን የቢዚነስ ቲዋይሲ ታክስ ሶፍትዌር አገልግሎትን እጅግ በጣም አነስተኛ

በሆነ ክፍያ በመጠቀም የሚከተሉትን ጥቅሞች ማግኘት ይችላሉ።

1. ጊዜን መቆጠቡ፣ እንግልት መቀነሱ

ፈይል ማገላበጥ ማስቀረቱ፣

ስሌቶችን እራሱ መስራቱ፣

ከወር ወር የሚገላበጡ መረጃዎችንና ገንዘቦችን እራሱ ክትትል (track) ማድረጉና፣

በርሶና በአካውንታንቶ መካከል ግልጽ መረጃ ልውውጥ መኖሩ።

2. የሂሳብ ስሌት ስህተቶችንና የደረሰኘ መጥፈት ማስወገዱ፣

3. ከፈተኛ የሆነ ገንዘብ ከማጥፋት መታደጉ፣

ከስህተቶች ነጻ በመሆንዎ ለገቢዎችም ሆነ ለአካውንታንት የሚከፈሉ አላስፈላጊ ወቺዎችን ማስወገዱ

4. ለኦዲት ዝግጁ ማድረጉ፣በሁሉም ቦታ ቢዝነስዎ ከርሶ ጋር መሆኑ።

አመታዊም ሆነ በተለያየ ግዜ መንግስት ለሚያደርገው የኦዲት ስራ ዝግጁ በመሆን ከፍተኛ የሆነን ግምታዊን

ክፍያ ማስቀረቱ።

Page 6: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

5

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ማሰናዳት

የ Business TYCታክስሶፍትዌርለመጠቀም

የBusinessTYC Tax ሶፍትዌር ለመጠቀም ምንም ቅድመ ሁኔታ የለውም። ከርስዎ የሚጠበቀው ኦንላይን በመግባት በመጀመሪያ አካውንት መክፋት ብቻ ነው።

አካውንት ለመክፈት የBusinessTYC Taxአድራሻን ማለትምwww.businesstyc.com/tax የኢንተርኔት ብሮዉዘር ላይ

ካስገቡ በኋላ ይህን ገፅ ያገኛሉ። (የቢዝነሰ ቲዋይሲን ሶፈትዌሮች በደንብ ለመጠቀም የጉግል ክሮምን ኢንተርኔት ብሮዉዘር

እንዲጠቀሙ እንመክራለን።)

አንዴ አካውንት ከፈጠሩ በኋላ ይሕን የታክስ ሶፍትዌር በመጠቀም እዚሁ ገጽ ላይ በመግባት የተጠቃሚ ስምና የሚስጥር ቃል ማስገባት እንዳለበዎ አይዘንጉ። በመሆኑም የተጠቃሚ ስምና የሚስጥር ቃልዎን መዘንጋት የለብዎትም።

ስዕል 1 የአካውንት መፍጠሪያ

በመቀጠልም ከላይ በምትመለከቱት ፎርም ላይ እነዚህን መረጃ ያሰገቡ:-

1. Full Name/ ሙሉስም፣

2. Phone Number/ ስልክቁጥር

■ የግሎትን ስልክ ቁጥር ቢያስገቡ ይመረጣል

Page 7: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

6

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

3. Email Address፣ ■ ትክክለኛ የኢሜል አድራሻ ካስገቡ ሲስተሙ የተለያዩ መረጃዎችን ይልክሎታል

4. User Name/ የተጠቃሚስም፣ ■ ሶፍትዌሩ ላይ ሎግኢን ለማድረግ የሚጠቀሙት ሰም ለምሳሌ የራስዎ ስም ሊሆን ይችላል።

5. Password/ የይለፍቃልበማስገባት፣

■ ይህ የሚስጥር ቃል ሶፍትዌሩ ላይ ሎግኢን ለማድረግ የሚጠቀሙት። ይህ ቃል ከስድስት(6)

ፊደላት ያላነሰ ሲሆን በሚስጥር ለራስዎ ብቻ መያዝ ይኖርቦታል።

6. በመጨረሻም “Create Account” የሚለውንቁልፍይጫኑ። ቀጥሎም ይህን ገጽ ያገኙታል እዚህ ፎርም ላይ የሚከተለውን መረጃ እናስገባለን

ስዕል 2 የድርጅት መረጃ ማስገቢያ

1. Company Name

2. TIN Number/የግብርከፋይመለያቁጥር/፣

■ የTIN Number ወይም የግብርከፋይመለያቁጥር ይህ ሲስተምም ሆነ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

መስሪያ ቤቱ ድርጅትዎን የሚለይበት ቅጥር ሲሆን ይህ ቁጥር 10 አሐዝ መሆን አለበት።

3. VAT Number፣

■ የድርጅቱን ቫት መለያ ቁጥር እዚህ ያስገቡ

4. Phone Number፣

■ ከላይ ከተጠቀሰው ቁጥር በተጨማሪ የመስሪያ ቤትዎን ስልክ ቁጥር ያሰገቡ

5. Business Type

Page 8: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

7

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

■ የተሰማሩበት የሰራ ዘርፍ

6. Sales Entry፦

Sales Entry የሴልስ ኢንትሪ ስናስገባ እንደ ድርጅታችን ሽያጭ ብዛት መምረጥ እንችላለን።

ሁለት አይነት አማራጮች አሉን

■ SUMMARY ከመረጥን የሽያጭ መረጃ የምናስገባዉ ከካሽ ሬጅስተር ወርሃዊ ሰመሪ

ነዉ (ብዙ የሽያጭ ደረሰኝ ላላቸዉ ድርጅቶች)።

■ EACH RECEIPT ከመረጥን እያንዳንዱን የሽያጭ ደረሰኝ ማስገባት አለብን

(ድርጅታችን የሚያካሂደው ሽያጭ አነስተኛ ከሆነ ይህን መምረጥ እንችላለን)።

7. Region

8. Kifle Ketema

9. Email

10. የድርጅትዎ አድራሻ /Address

11. ስለድርጅትዎ ማብራሪያ/Describe your Company

12. አስቀምጥ/Save

ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ካስገቡ በኋላ “Save”የሚለውን ቁልፍ በመጫን ወደ ዳታቤዝ(ቋጥ)ያስገቡ። አሁን በሚገባ አካውንት ፈጥረናል ድርጅቶንም መዝግበዋል። ከዚህ ቀጥሎ የድርጅታችንን እለታዊ መረጃ እናስገባለን።

Page 9: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

8

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

መረጃ ማስገቢያ ወርሃዊ የተእታ ሪፖርት ማዘጋጀት:- ወርሃዊ የተእታ ሪፖርት የሚዘጋጀዉ ከግዢ እና ሽያጭ መረጃ ነዉ። ስለሆነም ወርሃዊ

የተእታ ሪፖርት ለማዘጋጀት መጀመሪያ የድርጅታችንን ግዢ እና ሽያጭ ሲስተሙ ዉስጥ ማስገባት አለብን። ያስገባነዉን መረጃ

በመጠቀም ሶፍትዌሩ እራሱ ተእታ ሪፖርት ያዘጋጅልናል።

በቲዋይሲ ሶፍትዌር 3 አይነት ግዢ ማስገባት እንችላለን፦

የአገልግሎት ግዢ፣

የእቃ ግዢ ፣

ተእታ ያልሆኑ ግዢ።

እነዚህን የግዢ መረጃዎች ሰብስቦ መያዝና ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ማሳወቅ ግዴታ ነው። ይህን ሶፍትዌር ተጠቅመን

የግዢ መረጃን የምናደራጀው እንደሚከተለው ነው።

Page 10: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

9

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

የሀገር ውስጥ እቃ ግዢ

በግራ በኩል ካለዉ “ሜኑ ባር” “የአገር ዉስጥ የእቃ ግዢ” የሚለዉን ይምረጡ። ሲስተሙ ቀጥሎ የሚመለከቱትን ገጽ

ያመጣሎታል። ይህ ገጽ ላይ የሀገር ውስጥ እቃ ግዢዎችን ማደራጀት እንችላለን።

ስዕል 3የሀገር ውስጥ እቃ ግዢ ማደራጃ

ማስታወሻ: ቅጹ ላይ መረጃ ማስገባት ከመጀመሮ በፊት ማስተዋል የሚገባ

1. መረጃ የሚመዘግቡበትን ወር ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ)

2. መረጃ የሚመዘግቡበትን ዓ.ም ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ)

Page 11: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

10

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

የሀገር ውስጥ እቃ ግዢ ገጽ ላይ አስፈላጊ መረጃዎችን ይሙሉ፣ እነዚም መረጃዎች ግዢው ከተከናወነበት ደረሰኝ የሚገኙ

ሲሆኑ የሚከተሉትን ያጠቃላል።

3. ግዢ የፈፀሙበትን የድርጅት ስም፣

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣

የአገልግሎት ዋጋ ያስገቡ፣

4. ዊዝሆልዲንግ ታክስ ሲስተሙ እራሱ ይስራሎታል።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ)

5. ግዢ የተፈፀመበት የደረሰኝ ቁጥር

የተሰጠበት ቀን (ቀቀ/ወወ/አአአአ)

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ)

6. የማሽን ቁጥር

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 5 ላይ እንደተመለከተዉ)

7 ግዢዉ ዊዝሆልዲንግ ካለዉ ደግሞ

ዊዝሆልዲንግ ደረስኝ ቁጥር

ዊዝሆልዲንግ ደረስኝ የተስጠበት ቀን (ቀቀ/ወወ/አአአአ)

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 6 ላይ እንደተመለከተዉ )

8 በስህተት የገባን የግዢ መረጃ ማጥፋት

በእያንዳንዱግዢበስተቀኝመጨረሻላይያለዉን“አጥፋ”የሚለዉላይክሊክማድረግ

ሲስተሙእርግጠኝመሆኖንይጠይቆታል “Ok” የሚለዉን ክሊክ ማድረግ ሲስተሙ መረጃዉን

ያጠፋዋል (ከላይካለዉምስልተራቁጥር 7 ላይእንደተመለከተዉ )

9 ከአንድ በላይ የግዢ መረጃ ለማስገባት ”Add” ላይ ክሊክ ያድርጉ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 8 ላይ እንደተመለከተዉ )

10 መረጃዎን በሚገባ ካሰ ገቡ በሀላ በመቀጠል “Save”የሚለውን ክሊክ በማድረግ ይጨርሳሉ።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 9 ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 12: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

11

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

የሀገር ውስጥ አገልግሎት ግዢ

የሀገር ውስጥ አገልግሎት ግዢለማሰገባት በግራ በኩል ካለዉ “ሜኑ ባር”የአገር ዉስጥ አገልገሎት ግዢ የሚለዉን

ይምረጡሲስተሙ ቀጥሎ የሚመለከቱትን ገጽ ያመጣሎታል

ስዕል 4የሀገር ውስጥ አገልግሎት ግዢ

ማስታወሻ: ቅጹ ላይ መረጃ ማስገባት ከመጀመሮ በፊት ማስተዋል የሚገባ

1. መረጃ የሚመዘግቡበትን ወር ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ

እንደተመለከተዉ )

2. መረጃ የሚመዘግቡበትን ዓ.ም ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ

እንደተመለከተዉ )

Page 13: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

12

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

በመቀጠል:- የሀገር ውስጥ አገልግሎት ግዢ መረጃን ስናስገባ

ግዢ የፈፀሙበትን የድርጅት ስም፣

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣

የአገልግሎት ዋጋ፣

3. የእቃው የአገልግሎት ዋጋ ስናስገባ ዊዝሆልዲንግ መጠኑን ሲስተሙ ይስራልናል። ግዢያችን ከ500 ብር በላይ ከሆነ

ዊዝሆልዲንግ ደረስኝ መቁርጥ ይኖርብናል።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ )

4. ደረስኝ የተስጠበት ቀንና

የደረስኝ ቁጥር መመዝገብ ይኖርብናል።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ )

6. ግዢ የተፈፀመበት ድርጅት የማሽን ቁጥር፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 5 ላይ እንደተመለከተዉ )

7. ዊዝሆልዲንግ ደረስኝ የተስጠበት ቀንና

የዊዝሆልዲንግ ደረስኝ ቁጥር

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 6 ላይ እንደተመለከተዉ )

8. በስህተት ያስገባነው መረጃ ካለ/ማጥፋት የምንፈልገው መረጃ ካለ አጥፋ የሚለውን ቁልፍ እንጫናለን።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 7 ላይ እንደተመለከተዉ )

9. ተጨማሪ ግዢ ካሎት አዲስ ጨምር/Add የሚለውን ቁልፍ በመምረጥ ማስገባት ይችላሉ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 8 ላይ እንደተመለከተዉ )

8. በመጨረሻም አሰቀምጥ/Save/ የሚለውን በመምረጥ ”Data Base“ውስጥ ያስቀምጡ፡፡

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 9 ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 14: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

13

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ተ.እ.ታ ያልሆኑ /ተጨማሪ እሴት ታክስ/ (Non-VAT)

ተ.እ.ታ ያልሆኑ /ተጨማሪ እሴት ታክስ/(Non-VAT):- ማለትም ቫት ተመዝጋቢ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር

ግዢዎችን ስናከናውን የሚከተለውን ገልጽ እናገኛለን።

ስዕል 5ተ.እ.ታ ያልሆኑ /ተጨማሪ እሴት ታክስ/ (Non-VAT)

ማስታወሻ: ቅጹ ላይ መረጃ ማስገባት ከመጀመሮ በፊት ማስተዋል የሚገባ

መረጃ የሚመዘግቡበትን ወር ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ

እንደተመለከተዉ )

መረጃ የሚመዘግቡበትን ዓ.ም ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2ላይ

እንደተመለከተዉ )

Page 15: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

14

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

በመቀጠል:-

የሚከተለውን መረጃ ያስገቡ

ግዢ የፈፀሙበትን የድርጅት ስም፣

የእቃው/የአገልግሎት ዋጋ፣

3. አንዳንድ ድርጅቶችየግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላይኖራቸው ስለሚችል ከሌለው እናልፈዋለን።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ)

4. ዊዝሆልዲንግ ደረስኝ የተስጠበት ቀንና

የዊዝሆልዲንግ ደረስኝ ቁጥር

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ )

5.ግዢ የፈፀሙበት ደረሰ ቁጥር

ግዢ የፈፀሙበት ቀን

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 5 ላይ እንደተመለከተዉ)

6. ግዢ የተፈፀመበት ድርጅት የማሽን ቁጥር፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 6 ላይ እንደተመለከተዉ )

7. ዊዝሆልዲንግ ደረስኝ የተስጠበት ቀንና

የዊዝሆልዲንግ ደረስኝ ቁጥር

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 7 ላይ እንደተመለከተዉ )

8. በስህተት ያስገባነው መረጃ ካለ/ማጥፋት የምንፈልገው መረጃ ካለ አጥፋ የሚለውን ቁልፍ እንጫናለን።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 8 ላይ እንደተመለከተዉ )

9. ተጨማሪ ግዢ ካሎት አዲስ ጨምር/Add የሚለውን ቁልፍ በመምረጥ ማስገባት ይችላሉ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 9 ላይ እንደተመለከተዉ )

10. በመጨረሻም አሰቀምጥ/Save/ የሚለውን በመምረጥ ”Data Base“ ውስጥ ያስቀምጡ፡፡

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 10 ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 16: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

15

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

የሃገር ውሰጥ ሽያጭ

የሃገር ውሰጥ ሽያጭ:መረጃ ለመሰገባት በቅድሚያ የሃገር ውሰጥ ሽያጭ የሚለውን ይምረጡ በመቀጠል ይህን ገፅ

ያገኙታል።

ስዕል 6የሃገር ውሰጥ ሽያጭ

ማስታወሻ: ቅጹ ላይ መረጃ ማስገባት ከመጀመሮ በፊት ማስተዋል የሚገባ

1.መረጃ የሚመዘግቡበትን ወር ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

2.መረጃ የሚመዘግቡበትን ዓ.ም ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 17: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

16

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

በመቀጠል:- ሽያጭ የፈፀምንለትን የድርጅት ስም፣

የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣

የእቃው/የአገልግሎት ዋጋ፣

4.የእቃው/የአገልግሎት ዋጋ ስናስገባ ዊዝሆልዲንግ መጠኑን ሲስተሙ ይስራልናል።

ሽያጭ ያከናወነው ከ10,000 ብር በላይ ከሆነ እና ዊዝሆልዲንግ ከተቆረጥብን መረጃዉን መመዝገብ

ይኖርብናል።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ )

5.ሽያጭ የተፈፀመበት የደረሰኝ ቁጥር

የተሰጠበት ቀን

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 5 ላይ እንደተመለከተዉ )

6.ሽያጭ የተፈፀመበት/ድርጅት የማሽን ቁጥር፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 6 ላይ እንደተመለከተዉ )

7.ዊዝሆልዲንግ ደረስኝ የተሰጠበት ቀንና

የደረስኝ ቁጥር መመዝገብ ይኖርብናል።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 7 ላይ እንደተመለከተዉ )

8.በስህተት ያስገባነው መረጃ ካለ/ማጥፋት የምንፈልገው መረጃ ካለ አጥፋ የሚለውን ቁልፍ እንጫናለን።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 8 ላይ እንደተመለከተዉ )

9. ተጨማሪ ሽያጭ ካሎት አዲስ ጨምር/Add የሚለውን ቁልፍ በመምረጥ ማስገባት ይችላሉ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 9 ላይ እንደተመለከተዉ )

10.በመጨረሻም አሰቀምጥ/Save/ የሚለውን በመምረጥ ”Database“ ውስጥ ያስቀምጡ፡፡

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 10 ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 18: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

17

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ዊዝሆልዲንግ ታክስ

ዊዝሆልዲንግ ታክስ:ካስገባነው የግዢ ዶክመንቶች በመነሳት ዊዝሆልዲንግ ታክሱን ከሲስተሙ እናገኛለን።

ስዕል 7ዊዝሆልዲንግ ታክስ

በመቀጠል:- ዊዝሆልዲንግ ታክሰ ከላይ ካሰገባነው የግዢና ሽያጭ መረጃ በመነሳት ከታች የተዘረዘሩትን መረጃዎች

እናገኛለን።

1 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣

ግዢ የፈፀሙበትን የድርጅት ስም፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

2 ቫት የተከፈለበት መጠን

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ )

3 ዊዝሆልዲንግ መጠን 2%

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ )

4 ዊዝሆልዲንግ የደረሰኝ ቁጥር

ዊዝሆልዲንግ የተሰጠበት ቀን

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 19: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

18

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ተእታ ማመልከቻ /VAT REPORT/

ተእታ ማመልከቻ /VAT REPORT/:ከላይ ባስገባነው መረጃ በመነሳት ወርሃዊ መረጃዎቻችንን እናገኛለን በመቀጠል

PRINT ከማድረጋችን በፊት ማስተካከል የምንፈልገው ነገር ካለ የቫት ሪፖር ማስተካከያ ገጽ ላይ “Edit” የሚለውን ቁልፍ በመጫን

የሚከተለውን የቫት ማስተካከያ እናገኛለን። እዚህም ገጽ ላይ እንደ ገቨርመንት ቮቸር፣ የዜሮ ምጣኔ ያላቸዉ እቃዎች እና የአገልግሎቶች

ሽያጭ፣ የታክስ ምህረት ያገኙ አቅርቦቶችና የመሳሰሉ መረጃዎችን ቀጥታ ማካተት እንችላለን። ለመለጠ ለመረዳት የሚከተለውን ምስልና

ማብራሪያ ይመልከቱ።

Page 20: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

19

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ስዕል 8ተእታ ማመልከቻ /VAT REPORT/

Page 21: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

20

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

● የዜሮ ምጣኔ ያላቸዉ እቃዎች እና የአገልግሎቶች ሽያጭ ዋጋ።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

● ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ የሆነ ሽያጭ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

● የታክስ ምህረት ያገኙ አቅርቦቶች ዋጋ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

● የውጭ አገር ግዢ ግብእት ዋጋ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ )

● ልዩ ልዩ ወጪዎች ግብእት ዋጋ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ )

● የተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተከፈለበት ግዢ ወይም ተመላሽ የማይጠየቅባቸው ግብአት ዋጋ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ )

● ሌሎች በወሩ ዉስጥ የሚታሰቡ የተጣራ ተጨማሪ አሴት ታክስ ተከፋይ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ )

● ካለፈዉ ወር የዞረ ብልጫ ክፍያ

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ )

ከላይ የተጠቀሱት ማስተካከያዎች አስተካክለን ከጨረስን በኋላ ከገሱ ግርጌ ላይ የሚገኘውን አስቀምጥ/save ቀልፍ (ከላይ ካለዉ ምስል

ተራ ቁጥር 5 ላይ እንደተመለከተዉ ) እንጫነዋለን።

Page 22: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

21

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

Page 23: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

22

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ስዕል 9ተእታ ማመልከቻ /VAT REPORT/

Page 24: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

23

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ማስታወሻ: ቅጹ ላይ መረጃ ማስገባት ከመጀመሮ በፊት ማስተዋል የሚገባ

1.መረጃ የሚመዘግቡበትን ወር ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

2.መረጃ የሚመዘግቡበትን ዓ.ም ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ )

3.FRONT የሚለውን ቁልፍ ስንጫን የመጀመሪያ ገፅ እናገኛለን PRINT እናደርጋለን።

Page 25: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

24

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ማስታወሻ: ቅጹ ላይ መረጃ ማስገባት ከመጀመሮ በፊት ማስተዋል የሚገባ

1.መረጃ የሚመዘግቡበትን ወር ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

2.መረጃ የሚመዘግቡበትን ዓ.ም ያሰተውሉ (ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2ላይ እንደተመለከተዉ )

3. BACK የሚለውን ቁልፍ ስንጫን የጀርባውን ገፅ እናገኛለን PRINT እናደርጋለን

Page 26: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

25

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

በቀላሉ Print ማድረግ እንችላለን።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ )

በቀላሉ Edit ማድረግ እንችላለን።

የስራ ግብር

የሰራተኛውን የሰራ ግብር ለማሰገባት በግራ በኩል ካለዉ “ሜኑ ባር” የሰራ ግብር የሚለዉን ይምረጡ፡፡ ሲስተሙ ቀጥሎ

የሚመለከቱትን ገጽ ያመጣሎታል፡፡ በመቀጠል ከታች የተዘረዘሩትን መረጃ ያሰገቡ፡፡

ስዕል 10የስራ ግብር

Page 27: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

26

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

በመቀጠል:-የስራተኛውን የስራ ግብር ለመስራት የሚከተለውን መረጃ ማስገባት ይኖርብናል።

● የሠራተኛው ስም፣የአባት ስም፣ የአያት ስም

● የተቀጠሩበት ቀን፣

● ደመወዝ/ብር/ እናስገባለታለን የተቀረውን ሲስተሙ እራሱ ደምሮ ያስቀምጥልናል።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

የትራንስፖርት አበል፣

የስራግብር የሚከፈልበት የትራንስፖርት አበል፣

የትርፍ ሰዓት ክፍያ፣

ሌሎችጥቅማጥቅሞች፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ )

ጠቅላላግብርየሚከፈልበትገቢ፣

የስራግብር፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ )

የትምህርትየወጪመጋራትክፍያ፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ )

የተጣራተከፋይ፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 5 ላይ እንደተመለከተዉ )

የሠራተኛፊርማ፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 6 ላይ እንደተመለከተዉ )

መረጃዎችን በሚገባ ከመዘገብን በሃላ አስቀምጥ/save የሚለውን ቁልፍ መጫን

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 7 ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 28: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

27

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

በተጨማሪም እንደ ድርጅታችን ስራተኞች ብዛት ሌላ ጨምር /ADD PAGE/ እንለዋለን::

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 8 ላይ እንደተመለከተዉ )

የጡረታ መዋጮ

የጡረታ መዋጮ:ከላይ ባስገባነው የስራ ግብር መረጃ መሰረት የጡረታ መዋጮውን ከሲስተሙ እናገኛለን። የጡረታ

መዋጮውን ለማሰገባት በግራ በኩል ካለዉ “ሜኑ ባር” የጡረታ መዋጮ የሚለዉን ይምረጡ ሲስተሙ ቀጥሎ

የሚመለከቱትንገጽያመጣሎታል፡፡

Page 29: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

28

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

የጡረታ መዋጮ:የጡረታ መዋጮውን ለማስገባት ከላይ ካሰገባነው የስራ ግብር በቀጥታ ከታች የተዘረዘሩትን ከሲሰተሙ

እናገኛለን።

● የቋሚ የሠራተኛው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር

● የሠራተኛው ስም፣የአባት ስም፣ የአያት ስም

● የተቀጠሩበት ቀን፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ )

● ደመወዝ/ብር/ እናስገባለታለን የተቀረውን ሲስተሙ እራሱ ደምሮ ያስቀምጥልናል።

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2 ላይ እንደተመለከተዉ )

የሰራተኛው መዋጮ መጠን 7% ከሲሰተሙ እናገኛለን፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 3 ላይ እንደተመለከተዉ )

የአሰሪው መዋጮ መጠን11% ከሲሰተሙ እናገኛለን፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 4 ላይ እንደተመለከተዉ )

በአሰሪው የሚገባ ጥቅል መዋጮ 18%(ረ + ሰ)፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 5 ላይ እንደተመለከተዉ )

ፊርማ፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 6 ላይ እንደተመለከተዉ )

አጥፋ፣

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 7ላይ እንደተመለከተዉ )

Page 30: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

29

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

አስቀምጥ/save

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 8 ላይ እንደተመለከተዉ )

በተጨማሪም እንደ ድርጅታችን ስራተኞች ብዛት ሌላ ጨምር /ADD PAGE/ እንለዋለን::

(ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 9 ላይ እንደተመለከተዉ )

ተጨማሪ ድርጅቶችን/አካውንቶችን በመፈጠር ማስተዳደር የተለያየ ድርጅት ሂሳብ የምንስራ ከሆነ አዲስ ደንበኛ የሚለውን ቁልፍ በመጫን አዲስ ደንበኛ መፍጠር እንችላለን።

ሲስተሙን በመጠቀም ከአንድ በላይ የሆነ የድርጅት መረጃዎችን መመዝገብ እንችላለን።

ማስታወሻ፡ የተለያየ ድርጅት ሂሳብ ለመስራት/አካውንት ለመፍጠር ቀድመን ከፈጠርነው አካውንት ላይ አዲስ ደንበኛ

የሚለውን እንመርጣለን።

Page 31: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

30

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

1. ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 1 ላይ እንደተመለከተዉ ድርጅት የሚለውን ቁልፍ ሲጫኑ

2. በመቀጠል ከላይ ካለዉ ምስል ተራ ቁጥር 2ላይ እንደተመለከተዉ አዲስ ደንበኛ በመፍጠር ከአንድ በላይ ድርጅቶችን

ማሰተዳደር/ ሂሳብ መሰራት ይቻላል።

Page 32: Contents - WeDeliver - Delivery in Addis Ababa · Contents መግቢያ ... መረጃ በመነሳት ሶፍትዌሩ እራሱ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን

Business TYC Tax Software Manual | የቢዝነስቲዋይሲ የታክስ ሶፍትዌር አጠቃቀም

31

www.Businesstyc.com www.Businesstyc.com/tax Address: Mexico Kkare Building, Office#815 Mobile#: +251 912 000 013 or +251 115 575 253

ማስታወሻ:- በመጨረሻመም መረጃዎቻችንን በሚገባ ከመዘገብን በኋላ ወር ላይ ሙሉ መረጃ ማግኘት/PRINT ማድረግ

እንችላለን። ከታች የተዘረዘሩትን መረጃ PRINT እናደርጋለን።

● የሀገር ውስጥ እቃ ግዢ፣

● የሀገር ውስጥ አገልግሎት ግዢ፣

● ታ.እ.ታ ያልሆኑ /ተጨማሪ እሴት ታክስ/ ማለትም ቫት የሌላቸው(Non Vat) የሆኑ ግዢዎች፣

● የጡረታ መዋጮ፣

● ዊዝሆልዲንግ የሚለውን ፎርም PRINT እናደርጋለን።

ሙሉ ስም፣ ፊርማ፣ ቀን እንመዘግባለን።

የድርጅቱን ማህተም እናደርጋለን።